Fana: At a Speed of Life!

ካሪም ቤንዜማ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ ለመቀላቀል ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ አጥቂ ካሪም ቤንዜማ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢቲሃደን ለመቀላቀል ተስማማ፡፡

ቢቢሲ ማምሻውን ይዞት በወጣው መረጃ የባለንድኦር አሸናፊው ቤንዜማ ሪያል ማድሪድን በመልቀቅ ከአል ኢቲሃደ ጋር የ3 ዓመት ውል ፈጽሟል፡፡

የ35 ዓመቱ ቤንዜማ በሪያል ማድሪድ ቆይታው 5 የሻምፒዮንስ ሊግና 4 የላሊጋ ዋንጫዎችን ጨምር 25 ክብሮችን አሳክቷል፡፡

በሪያል ማድሪድ የ14 ዓመታት ቆይታው 354 ጎሎችን በማስቆጠር ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ቀጥሎ የክለቡ ሁለተኛው ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነው፡፡

ክርስቲያኖ ሮናልድ ለሪያል ማድሪድ 450 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን÷ በአሁኑ ሰዓት ለሌላኛው የሳውዲ ክለብ አል ናስር በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.