ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፖል ካጋሜ በመከላከያ እና በደኅንነት ባለሥልጣናት ላይ ድንገተኛ ለውጥ ማድረጋቸው ተሰማ

By Alemayehu Geremew

June 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሩዋንዳ ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ የመከላከያ እና የደኅንነት ሚኒስትሮችና አዛዦች ለውጥ ማድረጋቸው ተሰማ::

ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ በለወጧቸው ባለሥልጣናት ምትክ ÷ ጆቪኔል ማሪዛሙንዳን በመከላከያ ሚኒስትርነት ፣ ሌተናል ጄነራል ሙባራክ ሙጋንጋን ደግሞ በመከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦርነት ሾመዋቸዋል::

በተጨማሪም የሀገሪቱ የምድር ኃይል ዋና አዛዥ እና የመከላከያ ሠራዊቱ የመረጃና ደኅንነት በአዲስ አዛዥና ኃላፊ መተካታቸው ተሰምቷል፡፡

ሞዛምቢክን ለማገዝ በተሰማራው የሩዋንዳ ኃይል ላይም የአዛዦች ለውጥ ተደርጓል ነው የተባለው::

የሩዋንዳው ዘ ኒው ታይምስ እንደዘገበው ፥ ፕሬዚደንት ካጋሜ ባለፈው ሰኞ ምሽት ይፋ ያደረጉት ሹም-ሽር ያልተጠበቀና ድንገተኛ ነበር::