የሀገር ውስጥ ዜና

14ኛው የኢጋድ የመሪዎች ጉባዔ የፊታችን ሰኞ በጅቡቲ ይካሄዳል

By Meseret Awoke

June 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) 14ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የመሪዎች ጉባኤ በሚቀጥለው ሰኞ በጅቡቲ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ድርጅቱ እንዳለው በጉባዔው ላይ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና የሥራ ኃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

13ኛው የኢጋድ የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ በ2012 ዓ.ም መካሄዱ ይታወሳል፡፡