Fana: At a Speed of Life!

3ኛው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሣምንት መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)3ኛው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሣምንት በአዲስ አበባ መከበር ጀመረ፡፡

ክብረ-በዓሉ በጊዮን ሆቴል እየተካሄደ ያለው “የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ንቁ ተሳትፎ ለዘላቂ ሠላም ፣ ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና ለመልካም አስተዳደር ግንባታ በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡

እስከ ሰኔ 2 የሚቆየው ሥነ-ሥርዓት የሲቪል ማኅበረሰቡ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ማሳየትና የእርስ በእርስ ግንኙነትን ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል።

በዛሬው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የፍትኅ ሚኒስትሩ ዶር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ÷ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሀገራዊ ግንባታው እየተጫወቱት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።

አሁን ላይ መንግስት የፈጠረው ምቹ ሁኔታም ማኅበራቱ ይበልጥ እንዲንቀሳቀሱ አድርጓቸዋል ብለዋል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጂማ ዲልቦ በበኩላቸው ÷ ከለውጡ በኋላ ከ 2 ሺህ 600 በላይ አዳዲስ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡

አቶ ጂማ ዲልቦ ÷ ድርጅቶቹ በተለይም ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው ጦርነት የተጎዱ ማኅበረሰቦችን ከማገዝ አኳያ ሰፊ ሥራ መሥራታቸውን ገልጸዋል።

ለዘላቂ ሠላምና ሀገራዊ ግንባታ ሚናቸውን እንደሚወጡ ያላቸውንም ዕምነት ተናግረዋል፡፡

እየተከበረ የሚገኘው 3ኛው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሣምንት ማኅበራቱ በኢትዮጵያ ያላቸውን የማኅበረሰብ አገልግሎት ሚና ይበልጥ ለማጠናከር የሚረዳ እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል።

በታሪኩ ለገሠ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.