ኢራን ከድምፅ የፈጠነ ሚሳኤል መስራቷን ይፋ አደረገች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ኃይፐር ሶኒክ ሚሳኤል ሠርታ ለዕይታ አቀረበች፡፡
የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ÷ አዲሱ ኃይፐር ሶኒክ ሚሳኤል በቀጣናው ዘላቂ ደኅንነታችንን ለማረጋገጥ ይረዳናል ማለታቸውን አር ቲ ዘግቧል።
በፋርስ ቋንቋ “ፋታህ” ወደ አማርኛ ሲመለስ ደግሞ “ድል አድራጊ” ብለው የሰየሙትን ከድምፅ የፈጠነ ሚሳኤል የሀገሪቷ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተሰበሰቡበት በኢራኗ ዋና ከተማ ቴህራን ይፋ ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡
የኃይፐር ሶኒክ ሚሳኤሉ የመወንጨፍ ፍጥነት ለአዲሱ ትውልድ የሀገሪቷ ጦር የመጀመሪያው እንደሚሆንም የሀገሪቷ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አሚር አሊ ሃጂዛዴህ ÷ ስለ ሚሳኤሉ ዐቅም ዝርዝር ማብራሪያ ሠጥተዋል ነው የተባለው፡፡
እንደ ገለጻቸው ሚሳኤሉ 1 ሺህ 400 ኪሎ ሜትር ተወንጭፎ ዒላማውን በብቃት የመምታት ዐቅም አለው፡፡