የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪው አልሻባብ በኢትዮ-ሶማሊያ ድንበር አካባቢ ሊፈጽም የነበረው ጥቃት ከሸፈ

By Alemayehu Geremew

June 07, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የአልሸባብ ቡድን በዛሬው ዕለትበኢትዮ-ሶማሊያ ድንበር ዶሎ አካባቢ ሊፈጽም የነበረው የሽብር ተግባር ከሽፏል፡፡

ቡድኑ አጥፍቶ ጠፊ በማሰማራት በአካባቢው ጉዳት ለማድረስ ያደረገውን ሙከራ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት በተሳካ ሁኔታ አክሽፎታል፡፡

የሽብር የቡድኑ አባላት ይዘውት ከመጡት መሳሪያ ጋር መደምሰሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።