የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ምክትል ስራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

June 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ምክትል ስራ አስፈፃሚ ካርል ስካው ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍን ላልተገባ አላማ በማዋል ያጋጠሙ ችግሮችን ቀጣይ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ምክክር አድርገዋል፡፡

አምባሳደር ሽፈራው በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷መንግስት ሰብዓዊ ድጋፎችን ላልተገባ አላማ የሚያውሉትን አካላት አይታገስም ማለታቸውን በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡