Fana: At a Speed of Life!

ሪያል ማድሪድ እና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ  በቤሊንግሃም ዝውውር ሲስማሙ ሊዮኔል ሜሲ ወደ አሜሪካ ሊያቀና ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሪያል ማድሪድ እንግሊዛዊውን የቦሩሲያ ዶርትመንድ አማካይ ጁዲ ቤሊንግሃምን ለማስፈረም መስማማቱ ተሰምቷል።

ሎስብላንኮዎች አማካዩን ለማስፈረም 113 ሚሊየን ፓውንድ የሚከፍሉ ሲሆን፥ ተጫዋቹም ስድስት አመታት የኮንትራት ውል እንደሚፈርም ይጠበቃል።

ቤሊንግሃም ስሙ ከሊቨርፑል እና ሪያል ማድሪድ ሲያያዝ መቆየቱ ይታወሳል።

በሌላ በኩል የቼልሲው የመሀል ክፍል ተጫዋች ንጎሎ ካንቴ የሳዑዲውን ክለብ አል ኢቲሃድን ለመቀላቀል መስማማቱን ስካይ ስፖርትን ጨምሮ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው፡፡

በዝውውር ውሉ መሰረት ካንቴ 86 ሚሊዮን ፓውንድ (107 ሚሊየን ዶላር) አመታዊ ደመወዝ የሚከፈለው ሲሆን ተጨማሪ የምስል መብት ሽያጭ ገቢና ማበረታቻዎችን ያገኛል ተብሏል፡፡

የብራይተኑ አርጀንቲናዊ ተጫዋች አሌክሲስ ማክ አሊስተር ሊቨርፑልን ለመቀላቀል ተስማምቷል፡፡

በብራይተን ድንቅ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው ማክ አሊስተር ከአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫን ማንሳቱ አይዘነጋም፡፡

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲም የአሜሪካውን ኢንተር ሚያሚ እንደሚቀላቀል ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

ኢንተር ሚያሚ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር በምስራቁ ዞን ባለው ውድድር የወረደ አቋም እያሳዩ ከሚገኙ ክለቦች አንዱ ሲሆን በሊጉ ግርጌ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.