Fana: At a Speed of Life!

ጀርመን በተለያዩ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ጋር የምታደርገውን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደው የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ዮአኪን ፍላስባርዝ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴዔታ አለምአንተ አግደው እና ሚኒስትር ዮአኪን ፍላስባርዝ ጨምሮ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ባደረጉት ውይይት በሂደት ላይ የሚገኘውን ሀገራዊ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዝግጅት እንቅስቃሴዎችን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በጀርመን መንግስት ትብብር እየተከናወኑ በሚገኙ እንዲሁም ወደፊት በጋራ ትብብር ሊከናወኑ በሚገባቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ መምከራቸውም ነው የተገለጸው፡፡

በውይይት መድረኩ አቶ አለምአንተ አግደው ፥ በጀርመን መንግስት ትብብር በተካሄዱት እና በሂደት ላይ በሚገኙት የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ዝግጅትና የትግበራ፣ መደበኛ ያልሆነ የሰዎች ፍልሰትን ለማስቀረት ስለተከናወኑ፣ ሀገራዊ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዝግጅት ሂደት ላይ በትብብር እየተከናወኑ ስለሚገኙ ስራዎችንና ሌሎችን በማውሳት አመስግነዋል፡፡

ይህ ዓይነቱ ትብብር በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነትም ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትር ዮአኪን ፍላስባርዝ በበኩላቸው ፥ ጀርመን በግጭቱ ወቅትም ቢሆን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ትብብር ስታደርግ የነበረ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታው በተጠቀሱት እና በሌሎች የተመረጡ ጉዳዮች ላይ የጀርመን መንግስት ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የተናገሩት፡፡

በዚህ ረገድ በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ካደረጉት ድጋፍ በተጨማሪ የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን ጨምሮ የዲሞክራሲ ሂደትን ለማገዝ 10 ሚሊየን ዩሮ በትብብር ለመስጠት መወሰናቸውን ጨምረው መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.