Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

አይ ኤስ አይ ኤስ የሽብር ቡድንን ለማጥፋት የተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት የሚኒስትሮች ስብስባ ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ ጅዳ ተካሄዷል።

በስብስባው ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተሳተፉ ሲሆን ÷ከስብሰባው ጎን ለጎን ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡

በሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ስላለው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት፣የሽግግር ፍትሕ ሂደት፣የሰብዓዊ መብቶች እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮችላይ መወያየታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.