የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች ከተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

June 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሁሉም የእምነት ተቋማት ከተውጣጡ የሃይማኖት መሪዎች እና ከሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ ማምሻውን ከሁሉም የእምነት ተቋማት የሃይማኖት መሪዎች እና ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች ጋር ገንቢ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡

“በውይይታችንም÷ ሰላምን ለማፅናት በቁርጠኝነት በትብብር መስራት እንዳለብን ተስማምተናል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

“በኃይማኖቶች መካከል ያለውን ቅርበት እና ትብብር  ማጠናከር ሰላምን ከማፅናት ባለፈ ለጀመርነዉ ልማትም አስፈላጊ በመሆኑ ይህንኑ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናልም” ነው ያሉት፡፡