Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና አሜሪካ በዕርዳታ እህል ላይ የሚፈፀመውን ዝርፊያ ለመከላከል በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት በዕርዳታ እህል ላይ የሚፈፀመውን ዝርፊያ ለመከላከል በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት ዛሬ በጋራ መግለጫ መስጠታቸውን ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡
በመግለጫቸውም÷ በኢትዮጵያ እየተስተዋለ ያለውን የምግብ ዕርዳታ ዝርፊያ ችግር ለመፍታት ቁርጠኞች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ሁለቱ መንግስታት እንደዚህ ያሉ ወንጀለኞች በሕግ እንዲጠየቁ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ቀልጣፋ የእርዳታ ማከፋፈል ስርዓትን ለማስፈን በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ጠቁመዋል።
አሜሪካ እና ኢትዮጵያ የሀገራቱን ህዝቦች ጥቅም በሚያስቀድም መልኩ በጋራ ለመስራት ቁርጠኞች መሆናቸውንም ነው በጋራ በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.