Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 130 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማቀዱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መዳረሻውን ለማስፋት የሚያግዙትን 130 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማቀዱን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ኢስታንቡል በሚገኘው የአይ ኤ ቲ ኤ ኤ ጂ ኤም ፕሮግራም ላይ ከአቪዬሽን ዴይሊ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም ፥ አየር መንገዱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ካሳረፈበት ተጽዕኖ ሙሉ በሙሉ ማገገሙን ገልፀዋል፡፡

በዚህም አሁን ላይ መዳረሻውን የበለጠ ለማስፋት እየተሰራ እንደሆነም ነው የተናገሩት።

በዚህም አሁን ላይ ወደ 140 በሚጠጉ አውሮፕላኖች እየተሠራ እንደሆነ አመልክተው ፥ በፈረንጆቹ 2035 ቁጥሩን ወደ 271 አውሮፕላኖች በማሳደግ አገልግሎት ይሰጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ሥራ አስፈጻሚው አንስተዋል፡፡

ይህን ለማሳካትም 130 ተጨማሪ አውሮፕላኖች እንደሚታዘዙ አመላክተዋል።

በዚህም እድሜ የተጫናቸው አውሮፕላኖች መተካት ስለሚያስፈልጋቸው ይህ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

ከሰኔ 5 ቀን ጀምሮ አየር መንገዱ ከሚያዛቸው 29 አውሮፕላኖች ማለትም 17 የ737 ማክስ፣ አምስት 777ኤፍ ኤስ፣ አንድ 787-9 እና ሥድስት ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላኖች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

እየተጠናቀቀ ባለው በጀት ዓመት አየር መንገዱ 12 አዳዲስ አውሮፕላኖችን መረከቡ ታውቋል።

በአፍሪካ 63 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት አየር መንገዱ ፥ በአሁኑ ወቅት ያለውን 20 አውሮፕላን ማረፊያዎች ወደ 27 እንደሚያሳድግም ነው የተጠቆመው፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው አየር መንገዱ እየሰጠ ያለው የጭነት አገልግሎት ከፍተኛ ገቢ ለመሰብሰቡ ትልቅ አስተዋጽዖ እንዳደረገ አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.