ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ያለመ ሕዝባዊ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ያለመ ሕዝባዊ የንቅናቄ መድረክ በድሬዳዋ ከተማ ተካሄደ፡፡
በመርሐ ግብሩ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሼቴ፣ የምክር ቤት አባላት፣ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡
የንቅናቄ መድረኩ “በተጠናከረ የማኅበረሰብ ተሳትፎ ሕገ-ጥ የሰዎች ዝውውርን በጋራ እንከላከል” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በተለያዩ ዝግጅቶች የተካሄደው የሚገኘው፡፡
ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)÷ዜጎች በሀገር ውስጥ ሰርተው መለወጥን ልምድ ማድረግ አለባቸው፤ ከሀገር ውጭ መስራት ከፈለጉም መስፈርቱን በማሟላት በስራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል በውጭ ሀገር ስራ መሰማራት እንደሚችሉ አስገንዝበዋል፡፡
በሕገ-ወጥ መንገድ በመጓዝ ዜጎች ለአደጋ እንዳይጋለጡ ቤተሰብ፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከፍተኛ ድርሻ አላቸው ብለዋል፡፡
ዜጎችን ከስደት በመመለስ ደረጃ የተደረገው ጥረት በጎ ስራ መሆኑን ገልፀው÷ ቀጣዩ ሥራ ስደትን የሚፀየፍ እና ስራ ወዳድ የሆነ ወጣት ማፍራት ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት፡፡
በሕገ-ወጥ ዝውውር ሳቢያ ክብርና ስብዕናው የሚዋረድበትና በባርነት ቀንበር ተጠምዶ የሚማቅቅበት መሆኑንን ገልጸዋል፡፡