የሀገር ውስጥ ዜና

የዘር ወቅት ደርሶ የማዳበሪያ እጥረት ለገጠማቸው አከባቢዎች ቅድሚያ ማዳረስ ይገባል – ግብርና ሚኒስቴር

By Amele Demsew

June 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘር ወቅት ደርሶ አፈር የማዳበሪያ እጥረት ለገጠማቸው አከባቢዎች የዘር ወቅት ካልደረሰባቸው አከባቢዎች እንዲቀርብ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑንም የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ÷እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓም ግዢ የተፈጸመበት 12 ነጥብ 87 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ሙሉ በሙሉ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ግዢ ከተፈጸመበት 12 ነጥብ 87 ሚሊየን ኩንታል 6 ነጥብ 25 ሚሊየን ያህሉ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ከነበረው ክምችት ጋር በድምሩ 5 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል ብለዋል፡፡

2 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ በተለያዩ ህብረት ስራ ማህበራት መጋዘን እንደሚገኝና የዘር ወቅት ለደረሰባቸው እንዲከፋፈል እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የዘር ወቅት ደርሶ የማዳበሪያ እጥረት ለገጠማቸው አከባቢዎች የዘር ወቅት ካልደረሰባቸው አከባቢዎች እንዲቀርብ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በሃይለየሱስ ስዩም