በአማራ ክልል 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በክልሉ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል የታቀደ ሲሆን÷ እስካሁን ድረስ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱ ነው የተገለፀው።
በተጨማሪም 600 ሚሊየን የተከላ ጉድጓድ መዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡
ችግኞቹ በክልሉ የአፈር ለምነትን ለመጠበቅ፣ሀብት የሚያስገኙ እና ለምግብነት የሚውሉ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
የተዘጋጁ ችግኞችን ለመትከል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተሳታፊ እንዲሆን የክልሉ ግብርና ቢሮ ጥሪ ማቅረቡን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡