በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለአረንጓዴ አሻራ ልማት 55 ሚሊየን ችግኝ ተዘጋጀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ ልማት የሚውል 55 ሚሊየን ችግኝ መዘጋጀቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ባበክር ከሊፋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ÷ የተዘጋጀው ችግኝ ባለፈው የበጋ ወቅት የአፈርና ውሃ ጥበቃ የተካሄደበት 29 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የሚተከል ነው።
ችግኙ በአምስተኛው ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር መሰረት በማድረግ የሚከናወን እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡
የሚተከሉት ችግኝ የተፈጥሮ ኃብት መልሶ እንዲያገግም የሚያግዙ ከመሆናቸው ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የቡና፣ የማንጎ፣ የአቮካዶ፣ ቀርከሃን ጨምሮ ሌሎች ሀገር በቀል ችግኞች እንደሚገኙበት አመልክተዋል፡፡
በክልሉ ባለፈው ክረምት ከተተከለው 42 ነጥብ 3 ሚሊየን ችግኝ ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ መጽደቁን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!