ስፓርት

የሀድያ ሆሳዕና እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

By Feven Bishaw

June 09, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ከተማ 3ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ጥሩ ፉክክር በታየበት በዚህ ጨዋታ አዳማ ከተማ 3 ለ 0 እየመራ ቢቆይም ሀድያ ሆሳዕና ነጥብ መጋራት ችሏል።

በጨዋታው የአዳማ ከተማን ሁለት ግቦች ዳዋ ሆቴሳ ሲያስቆጥር ቀሪዋን አንድ ግብ አዲስ ተስፋዬ አስቆጥሯል፡፡

የሀድያ ሆሳዕናን ሁለት ግቦች ደግሞ ባዬ ገዛኸኝ ያስቆጠረ ሲሆን ፥ አንዷን ግብ ሠመረ ሀፍተይ ማስቆጠር ችሏል፡፡