Fana: At a Speed of Life!

የማዳበሪያ አቅርቦቱ የዘር ወቅት ሳያልፍ እንዲሠራጭ አቅጣጫ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ እና አርሲ ዞኖች የዘር ወቅት ሳያልፍ የማዳበሪያ አቅርቦት ሥርጭት እንዲጠናቀቅ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከግብርና ሚኒስቴር ያዋቀረው የኢንስፔክሽን ቡድን በተጠቀሱት ወረዳዎች እና ዞኖች አስፈላጊው ክትትል እንዲደረግም አሳስቧል፡፡

ቡድኑ በተጠቀሱት አካባቢዎች የታዩትን ጠንካራና ደካማ ጎኖች ለይቶ ለክልሉ ግብርና ቢሮ አመራሮች ግብረ-መልስ መሥጠቱን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ የማዳበሪያ አቅርቦት ዕቅድ 9 ሚሊየን 244 ሺህ 210 ኩንታል እንደነበርና እስካሁን የቀረበው ደግሞ 4 ሚሊየን 706 ሺህ 49 ኩንታል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ከቀረበው የማዳበሪያ አቅርቦትም 73 በመቶ ያህሉ ለአርሶ አደሮች መሰራጨቱ በግብረ-መልሱ ተነስቷል።

ምልከታ በተደረገባቸው የምሥራቅ ሸዋ ወረዳዎች በሆኑት ሎሜ፣ አዳማ እና አደአ ÷ የቀረበላቸውን ማዳበሪያ ማሰራጨት መጀመራቸው ተነስቷል፡፡

በአርሲ ዞን ሄጦሳ እና ሎዴ ሄጦሳ ወረዳዎች በመሰረታዊ ኅህብረት ሥራ ማኅበራት የቀረበ ማዳበሪያ አለመኖሩም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ኢንስፔክሽን ቡድኑ ÷ ማዳበሪያ የቀረበላቸው ወረዳዎችና ዞኖች ሥርጭቱን በአፋጣኝ ማጠናቀቅ እንዳለባቸውና ያልቀረበውን ማዳበሪያ በሚመለከት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የዘር ወቅቱ ሳያልፍ እንዲቀርብ አስፈላጊውን ክትትል እንዲደረግ አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.