Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሩጫ ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ለሜቻ ግርማ በፓሪስ ዳይመንድ ሊግ የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሩጫ ውድድር  የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸንፏል፡፡

አትሌት ለሜቻ ርቀቱን በ7 ደቂቃ 52 ሰከንድ 11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ክብረ ወሰን በመስበር ያሸነፈው፡፡

በዚህም በኬንያዊው አትሌት በ7 ደቂቃ 53 ሰከንድ 63 ማይክሮ ሰከንድ ተይዞ የቆየውን የርቀቱን ክብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል፡፡

በሌላ በኩል ትናንት ምሽት በተካሄደው የፓሪስ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር አትሌት ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

ሌላኛዋ አትሌት እጅጋየሁ ታየ ደግሞ በርቀቱ 3ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኬንያዊቷ አትሌት ፉቲ ኪፕዮገን ርቀቱን 14 ደቂቃ 05 ሰከንድ 20 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በቀዳሚነት በማጠናቀቅ የዓለም ክብረ ወሰን መስበር ችላለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.