Fana: At a Speed of Life!

በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር 105 የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የ105 የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የአስተዳደሩ የትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

 

የመምሪያው ሃላፊ አቶ ሰይፉ ሞገስ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በብሄረሰብ አስተዳደሩ በርካታ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች በመሆናቸው ለትምህርት ጥራት መጓደል መንስኤ ሆነዋል።

 

በተለይም በሰሃላና ዝቋላ ወረዳዎች በ11 የዳስና የዛፍ ጥላ ስር ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

 

በብሄረሰብ አስተዳደሩ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ገጽታ ለመቀየርና የትምህርት ጥራትን ለማምጣት የመማሪያ ክፍሎቹ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።

 

ከግንባታዎቹ ውስጥ ከ30 በላይ የዳስ ጥላ ስር መማሪያ ክፍሎች ደረጃውን ወደ ጠበቀ ትምህርት ቤት መቀየር እንደሚገኝበት ሃላፊው ጠቁመዋል።

 

እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት በደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች 75 የመማሪያ ክፍሎች በመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም መርሐ ግብር አማካኝነት ግንባታቸው እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

 

ግንባታው በትምህርት ሚኒስቴር፣ ከተለያዩ ተቋማት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍና በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.