Fana: At a Speed of Life!

ቅንጅታዊ አሰራርን በማሻሻል በተሰራ ስራ 5 ቢሊየን ብር የሎጅስቲክስ ወጪን ማዳን መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሶስት አመታት በሎጅስቲክስ ዘርፉ ቅንጅታዊ አሰራርን በማሻሻል በተሰራ ስራ 5 ቢሊየን ብር የሎጅስቲክስ ወጪን ማዳን መቻሉን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

 

“የሎጅስቲክ ብቃት መሻሻልና የተቋማት ቅንጅት ለዘላቂ የኢኮኖሚ የትራንስፎርሜሽን” በሚል መሪ ሃሳብ የሎጅስቲክስ ዘርፍ ግንዛቤ ማስጨበጫና የባለድርሻ አካላት የምክክር አውደ ጥናት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

 

ያለው የሎጅስቲክስ አቅም ከገቢና ወጪ ንግድ እድገት ጋር ሲነፃፀር በብዙ ፈተናዎች የታጠረ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

 

ሚኒስትሩ ችግሩን ለመቅረፍ ጥናት እና ትንተናዎች መካሄዳቸውን ጠቅሰው፥ የብሄራዊ ሎጅስቲክስ ስትራቴጅ ተዘጋጅቶ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፀደቀ ከሶስት አመት በላይ ማለፉን ገልጸዋል።

 

በእነዚህ አመታት በቅንጅት በተሰራ ስራም 5 ቢሊየን ብር የሎጅስቲክስ ወጪን ማዳን ተችሏል ብለዋል።

 

አሁንም ዘርፉ አድጎ በሀገር ኢኮኖሚ እድገት አሻራውን እንዲያሳርፍ በዘርፉ ላይ የተሟላ ግልፅነትና ዘርፉን ለማሻሻል አቅምን ማሳደግ፣ አደረጃጀቶችን መፈተሽ እና አሰራሮችን መከለስ ያስፈልጋል ብለዋል።

 

በአውደ ጥናቱ የተለያዩ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።

 

በሳሙኤል ወርቃየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.