Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በ10 ሚሊየን ዶላር የጫማ ምርት የአቅም ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ ሊሆን ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኮሪያው ቡሳን ኢኮኖሚ ማስተዋወቂያ ኤጀንሲ በኢትዮጵያ በ10 ሚሊየን ዶላር የጫማ ምርት የአቅም ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ ሊያደርግ ነው።

 

ለአራት አመት የሚተገበረው ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በዘርፉ ለተሰማሩ ሀገር በቀል ጫማ ፋብሪካዎች እና ሰራተኞች ተወዳዳሪነታቸውን ማሳደግ የሚያስችል ቴክኒካል ድጋፍ እና አስፈላጊውን ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ታውቋል።

 

በደቡብ ኮሪያ ቡሳን ከተማ የጫማ ምርት የአቅም ግንባታ ፕሮጄክት ማስጀመሪያ እና በቡሳን ኢኮኖሚ ማስተዋወቂያ ኤጀንሲ የጫማ ኢንዱስትሪ ማስተዋወቂያ ማዕከል እና በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።

 

ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት እና ትብብር ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.