Fana: At a Speed of Life!

በትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከሞጣ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከከባድ ገልባጭ መኪና ጋር ተጋጭቶ የ10 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

አደጋው ከንጋቱ 11 ሰዓት ከ30 ከሞጣ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ለመንገድ ሥራ ጌጠኛ ድንጋይ ጭኖ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ይጓዝ ከነበረ ከባድ ገልባጭ መኪና ጋር ተጋጭቶ የደረሰ ነው።

በአደጋው የአውቶብሱን ሾፌር ጨምሮ የ10 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተመስገን ይበልጤ ተናግረዋል።

የገልባጭ መኪናው ሾፌርና ረዳት አለመገኘታቸውንም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሞጣ እና ግንደወይን ከተማ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

በአደጋው ሳቢያ አምስቱ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፥ የከፋ ጉዳት የደረሰበት አንድ መንገደኛ ባሕር ዳር ጥበበ ግዮን ሆስፒታል ለተሻለ ሕክምና መላኩም ታውቋል።

በሰላም አሰፋ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.