Fana: At a Speed of Life!

የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመረጠንን ሕዝብ ዝቅ ብለን በማድመጥ ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጡ ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ከመዲናዋ ነዋሪዎች ጋር በተደረጉ ሰፋፊ ውይይቶች የተነሱ ጥያቄዎች እና ቅሬታዎችን አጣርቶ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ያለአግባብ ታጥረው በተያዙ ቦታዎች፣ ያለ ልማት ታጥረው የተያዙና ግንባታቸው ተጀምሮ ለረጅም ጊዜ የቆሙ ህንፃዎች ፣ የመንግስት መኖሪያ ቤቶች ፣በከተማ ደረጃ የተፈጠሩ የስራ ዕድሎች የከተማዋን ነዋሪ በፍትሃዊነት ተጠቃሚ አለማድረጋቸውን ዛሬ ገምግመናል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ ባለፈም የኑሮ ጫናን ለመቀነስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እና የገቢ አሰባሰብ ስራ ኦዲት መገምገሙን አብራርተዋል፡፡

በዚህም ህዝቡ ያነሳቸው ቅሬታዎች ትክክል መሆናቸውን አምነናል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

በቀጣይነትም የመረጠንን ሕዝብ ዝቅ ብለን በማድመጥ ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጡ ስራዎች መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.