Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ቡድኖቹ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ዛሬ ያደረጉት የ26ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን ግቦች ቸርነት ጉግሳ በ13ኛው እና አቤል ያለው በ58ኛው ደቂቃ ላይ አስቀጥረዋል፡፡
የባህር ዳር ከተማን ግቦች ደግሞ አለልኝ አዘነ በ30ኛው እና ፍራኦል መንግስቱ በመጀመሪያው አጋማሽ በባከነ ሰዓት ማስቆጠር ችለዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.