Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ከ8 ሺህ በላይ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀዋል- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት 8 ሺህ 341 የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡

አቶ ሽመልስ ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞን ለማረጋገጥና ዜጎች በሁሉም ዘርፍ ያለቸውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በዚህ መሰረትም የክልሉን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ማሳደግና ማስፋፋት ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጀት እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በ2015 በጀት ዓመትም የ8 ሺህ 341 የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቁ አንስተው÷በዚህም 2 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል፡፡

በቀጣዩ በጀት ዓመትም የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.