የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 26 ቀን ጀምሮ ይሰጣል

By Tamrat Bishaw

June 10, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2015 የትምህርት ዘመን ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከፊታችን ሰኔ 26 ቀን ጀምሮ እንደሚሰጥ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረትም ወላጆች፣ መምህራን እና አመራሮች በቀሪ ጊዜያት ለተፈታኝ ተማሪዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል፡፡

ተማሪዎችም በፈተናው አመርቂ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ቀሪ ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡