Fana: At a Speed of Life!

ዴሞክራቲክ ኮንጎ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ቲሺኬዲ ገለጹ፡፡

አምባሳደር ፍርቱና ዲባኮ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ቲሺኬዲ አቅርበዋል፡፡

አምባሳደሯ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ፍርቱና÷ኢትዮጵያ ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር በባህል እና ሕዝብ ለሕዝብ ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደምትፈልግ ገልፀዋል።

ፕሬዚደንት ቲሺኬዲ በአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበርነታቸው ወቅት በሕዳሴ ግድብ የሶሰትዮሽ ድርድር ሂደት ላበረከቱት በጎ አስተዋፅኦም ምስጋና አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ቲሼኬዲ በበኩላቸው÷ በኮንጎ እና በኢትዮጵያ መካከል በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ያለው ግንኙነት እንዲጠናከር የመንግስታቸው ፍላጎት እንደሆነ መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.