Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትግራይ ክልል ከ510 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትግራይ ክልል ከ510 ሚሊየን ብር በላይ የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

በመቀሌ ከተማ ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ የከተማ አስተዳደሩ ህዝቡንና በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር ከ218 ሚሊየን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብና የተለያዩ ቁሳቁሶች በአጠቃላይ ከ510 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ለተፈናቃዮች ድጋፍ የሚውሉ የአልባሳት እና የምግብ ፣ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ስላለባቸው ለትምህርት ዘርፍ ለሚውሉ ፣ ለጤና እና ለቢሮ ግብዓቶች ድጋፎች ቅድሚያ መስጠቱንም ነው የገለጹት።

ከሰላም እንጂ ከጦርነት ትርፍ ስለማይገኝ ሰላማችንን ማጽናት አለብን ያሉት ከንቲባዋ ፥ በባለፈው ጦርነት የተጎዳነው ሁላችንም ነን ብለዋል።

በየትኛው የሀገሪቱ ጫፍ የሚያጋጥም ጉዳት የሁሉም ጉዳት በመሆኑ የወደመውን በትብብር መልሰን እንገነባለን ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ህዝቡ የፍቅር መልዕክቱን ልኳል ሲሉም ነው የተናገሩት።

የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቃል በገባው መሠረት ለትግራይ ክልል ድጋፍ ለማድረግ ቅድሚያ ተነሳሽነቱን ወስዶ ተግባራዊ በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል።

ተጋግዘን በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ወደ ልማትና እድገት መመለስ አለብን ማለታቸውን ኤኤም ኤን ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትግራይ ክልል ለሚያስገነባው ትምህርት ቤትም ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.