Fana: At a Speed of Life!

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት አጀንዳ የማሰባበሰብ ስራ ለማከናወን ጋምቤላ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያን (ፕ/ር) ጨምሮ ሌሎች የኮሚሽኑ አባላት አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ለማከናወን ጋምቤላ ገብተዋል።

አባላቱ ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የጋምቤላ ክልል ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

ዋና ኮሚሽነሩ በጋምቤላ በሚኖራቸው ቆይታ÷የአጀንዳ ልየታ ተሳታፊዎችን ማስመረጥ እና በክልል ደረጃ አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ እንደሚያካሂዱ ተገልጿል፡፡

ሀገራዊ ምክክሩ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ የላቀ ድርሻ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

መንግሥት በኢትዮጵያ ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት እና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በማሰብ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሙ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.