Fana: At a Speed of Life!

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ3 ሚሊየን ተሻግሯል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ3 ሚሊየን በላይ ሆኗል።

ዕለታዊ የኮሮና ቫይረስ አሃዞች እንዳመለከተው በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 207 ሺህ 94 ደርሷል።

እንዲሁም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 882 ሺህ 552 መድረሱ ነው የተነገረው።

በአሜሪካ 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው 987 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 55 ሺህ 415 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በስፔን 23 ሺህ 190 ፣ በጣሊያን 26 ሺህ 44 ፣ በፈረንሳይ 22 ሺህ 856 እንዲሁም በብሪታኒያ 20 ሺህ 732 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.