Fana: At a Speed of Life!

ኔቶ በታሪኩ ትልቅ ያለውን የአየር ልምምድ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በታሪኩ ትልቅ ያለውን የአየር ልምምድ በጀርመን ሊያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የአየር ልምምዱ የሩሲያን ጦር ለመመከት ያለመ ስለመሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

ከ74 ዓመታት በኋላ በሚደረገው በዚህ የአየር ልምምድ ከ250 በላይ አውሮፕላኖች እና ከ25 ሀገራት የተውጣጡ 10 ሺህ አባላት ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

የአየር መቃወሚያ ልምምዶች ከዛሬ ጀምሮ እስከፈረንጆቹ ሰኔ 23 ድረስ የሚደረግ ሲሆን ኔቶ በሩሲያ ላይ ያለውን የመከላከል አቅም ለማጠናከር እና በአባላቱ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በሉላ በኩል ልምምዱ በሚቀጥለው ወር በሉቴኒያ ቪልኒየስ በሚካሄደው የኔቶ ስብሰባ ላይ ሩሲያን በተመለከተ ቅደመ አጀንዳ ለማስቆመጥ ስለመሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡

ከተሳታፊ የጦር አውሮፐላኖች መካከል ግማሽ ያህሉ የአሜሪካ ሲሆኑ አሜሪካ በልምምዱ 100 ያህል አውሮፕላኖችን ወደ አውሮፓ እንደምትልክ ተገልጿል፡፡

በልምምዱ ላይ የሚሳተፉት ወታደሮች ከፈረንጆቹ ግንቦት 29 ጀምሮ ወደ አውሮፓ መግባታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.