የኮሮና ቫይረስ ትምህርት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደረሰ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት የወደፊት ዕጣ ፈንታን የሚመለከተው ዓለም አቀፉ የባህል ተቋም ዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ኮሚሽንን 2ኛ ስብሰባ ተካሂዷል።
በዚህም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆኖነዋል።
በውይይቱም የኮረሮ ቫይረስ በትምህርትና ልማት ላይ በረጅም ጊዜ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ለማዘጋጀት መግባባት ላይ መደረሱን ከፕሬዚዳንት ፅሀፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።