አቶ አወል አርባ በኢትዮጵያ ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ተወካይ ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በኢትዮጵያ ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ተወካይ ፋራይ ዚምዲዚ ጋር በአካባቢው ልማት ዙሪያ በሠመራ ከተማ ተወያዩ፡፡
የድርጅቱ ተወካይ የክልሉ የእርሻ ልማት እንቅስቃሴን ከጎበኙ በኋላ በዘርፉ ድጋፍ በሚያደርጉበት ዙሪያ ከአቶ አወል ጋር መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አቶ አወል የድርጅቱ ተወካይ በክልሉ በቀጣይነት በእርሻ ዘርፍ ለሚያደርጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።
ድርጅቱ በሠመራ ከተማ አቅራቢያ ለእርሻ ስራ እና ከዚሁ ተግባር ጋር ለተያያዙ ግንባታዎች የሚውል 2 ሺህ 550 ካሬ ሜትር ቦታ መረከቡም ተገልጿል፡፡
ፋራይ ዚምዲዚ በክልሉ በሚያደርጉት የሦስት ቀናት ጉብኝት በእርሻ ዘርፍ የተሰሩ ተግባራትን እንደሚመለከቱ ይጠበቃል፡፡
በዚህም ቀደም ሲል በድርጅታቸው ድጋፍ የተሰሩ ፕሮጀክቶችና ማሳዎችን የሚጎበኙ ይሆናል፡፡
በነበረው ችግር ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የእንሰሳት አቅርቦትና ህክምና እንደሚሰጥም ተመላክቷል፡፡