በተለያዩ ክልሎች የአመራሮች የውይይት መድረክ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማን ጨምሮ የአማራ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሐረሪ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ ሲዳማ፣ ሶማሌ እና አፋር ክልሎች የአመራሮች ውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።
መድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴና ማዕከል ኮሚቴ ባስቀመጡት አቅጣጫ ላይ የጋራ አረዳድ በመፍጠር የአስተሳሰብና የተግባር መሰናሰልን ከፍ ለማድረግ ብሎም ስኬቶችን ለማስቀጠልና ፈተናዎችን ለመመከት ያለመ ነው ተብሏል።
መድረኩ ስኬቶችን በመገንዘብ፣ የፈተናዎችን መነሻና መፍትሔ በመረዳት ስኬቶችን የማስቀጠልንና ፈተናዎችን የመቋቋምን ፅናት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚያስችል መገለጹን የየክልሎቹ ኮሙኒኬሽን ቢሮዎች መረጃ ያመላክታል፡፡
እንዲሁም መድረኩ የመተራራም፣ የመገነባባትና የመተጋገዝ መንፈስን መሠረት ያደረገ ትግል የሚካሄድበት መሆኑ ተገልጿል፡፡