የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 50 ደርሷል

By Tibebu Kebede

April 27, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 50 መድረሱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ943 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል።

በዚህም አንድ ሰው የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ሲሆን፥ የ45 አመት ትውልደ ኢትዮጵያዊ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

ግለሰቡ ከእንግሊዝ የተመለሰና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ ነው ተብሏል።

69 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ህክምና ውስጥ ናቸው።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።