Fana: At a Speed of Life!

15 የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በጊዜያዊነት ታገዱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 15 የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በጊዜያዊነት መታገዳቸውን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ÷የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ በላይ የዜጎችን መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ በርካታ ተግባራት እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ በሕግ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዜጎችን ለሥራ ስምምነት ወደተደረሰባቸው መዳረሻ ሀገራት ለመላክ ፈቃድ በመውሰድ ወደ ሥራ እንዲገቡ እንደሚደርግ አስረድቷል፡፡

ፈቃድ ወስደው የሚሰሩ ኤጀንሲዎችም በአዋጅ ቁጥር 923/08 እና በማስፈፀሚያ መመሪያ መሰረት ሊያሟሉ የሚገባቸውን እና አጠቃላይ እንቅስቃሴያቸውን ለሚኒስቴሩ ማሳወቅ እንደሚገባቸው አብራርቷል፡፡

ይሁን እንጂ ከጥቅምት 14 ቀን 2015 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ 15 ኤጀንሲዎች ለሚኒስቴሩ ምንም አይነት ሪፖርት አለማድረጋቸውን ነው የገለጸው፡፡

በአዋጅ ቁጥር 923/08 መሰረት ድርጊቱ የሥራ ፈቃድ ስረዛ የሚያስከትል ቢሆንም ሚኒስቴሩ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን ሲሰጥ መቆየቱን ገልጿል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎ ከድርጊታቸው መማር እንዲችሉ ከግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለሦስት ወራት መታገዳቸውን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.