የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ በቢጫ ወባ በሽታ 86 ሰዎች ተይዘዋል – የጤና ሚኒስቴር

By Tibebu Kebede

April 27, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በቢጫ ወባ በሽታ 86 ሰዎች መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አነሞር እና ኤነር ወረዳ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ የበሽታው ምልክት መታየቱን ሪፖርት መደረጉን ገልፀዋል።