Fana: At a Speed of Life!

በኅብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ዙሪያ ለ5 ዓመታት የሚተገበር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኅብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ዙሪያ ለአምስት ዓመታት የሚተገበር ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል፡፡

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና የማኔጅመንት ሳይንስ ፎር ሄልዝ የተባሉ ድርጅቶች አማካኝነት ተግባራዊ እንደሚደረግም ተጠቅሷል፡፡

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ሥርዓትን እና በሽታ የመከላከል አቅምን ለመገንባት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ለፕሮጀክቱ ትግበራ የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት 12 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉ ነው የተገለጸው፡፡

ፕሮጀክቱ በኦሮሚያ፣ በደቡብ እና በአማራ ክልሎች በተመረጡ 12 ወረዳዎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር እንደሚተገበር ተጠቁሟል፡፡

በዚህም ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው አካባቢዎች የኅብረተሰቡን የጤና ችግር መፍታት እና ከባድ የጤና ችግሮች ሲያጋጥሙ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ ተግባራዊ የሚሆንባቸው ወረዳዎች የተመረጡት ባላቸው የበሽታ ተጋላጭነት፣ ከዚህ በፊት በተደረጉ የጤና ሪፖርቶች እና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች መሆኑም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት ሚሽን ዳይሬክተር ቲሞቲ ስቴን፣ በኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማህበር የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.