የግብርና ሚኒስትሩ ከኔዘርላንድስ የውጭ ንግድና ልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) በኔዘርላንድስ የውጭ ንግድና ልማት ትብብር ሚኒስትር ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ፡፡
ኔዘርላንድስ ከኢትዮጵያ ጋር ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ያላት አገር ስትሆን÷በተለይም በግብርናው ዘርፍ የላቀ የልማት ትብብር ዋነኛ አጋር መሆኗ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ስራ እየተከናወነ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና እና ስርዓተ ምግብን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ የአትክልትና ፍራፍሬ እሴት ሰንሰለት በተጨማሪ በወተት፣ በማርና አሳ ሃብት ምርትና ምርታማነት እሴት ሰንሰለት ላይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተነስቷል፡፡
በውይይቱ የኔዘርላንድስ የውጭ ንግድና ልማት ትብብር ሚኒስትር ሊስጄ ስችሬንማቸር÷በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር ሄንክ ጃን ባከር እና ሌሎች ተወካዮች መሳተፋቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡