Fana: At a Speed of Life!

ለኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ለመተንፈሻ አገልግሎት የሚውል መሣሪያ በመላ ሀገሪቱ እየተስራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ለመተንፈሻ አገልግሎት የሚውል መሣሪያ እየተስራጨ ነው።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለኮቪድ 19 አገልግሎት የሚውሉ የኦክስጅን ሲሊንደሮች ስርጭት እያካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመላው ሃገሪቱ ለሚገኙና የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለማከም በተመረጡ 31 ሆስፒታሎች፣ 9 ጤና ቢሮዎች እና ለ2 ከተማ መስተዳድሮች 3 ሺህ 322 ብዛት ያላቸው የመተንፈሻ ሲሊንደሮች በማሠራጨት ላይ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

እየተሰራጩ ያሉት አምስት አይነት የኦክስጅን ሲሊንደሮች ሲሆን፥ አንዱ ለአምቡላንስ አገልግሎት ቀሪዎቹ ደግሞ በኮቪድ 19 ተኝቶ ታካሚዎች የሚውል ነው፡፡

የኦክስጅን ሲሊንደር አንድ ታካሚ በቂ ኦክስጅን ወደ ሠውነቱ ማስገባት ሲያቅተው ኦክስጅን ሠውነቱ ውስጥ እንዲገባ የሚረዳ የሕክምና መርጃ መሣሪያ ነው።

ሲሊንደሮቹ 9  ሚሊየን 442 ሺህ ብር ወጪ እንደተደረገባቸው ተመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.