Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከካናዳ ጋር በንግድ ዘርፍ  ያላትን ግንኙነት ለማጎልበት ቁርጠኛ መሆኗን ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከካናዳ ጋር ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ÷ በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ስቴፋን ጆቢንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይቱ ሁለቱ አገራት የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ የሁለትዮሽ እና የባለ ብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከካናዳ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ትብበር በተለይም በፖለቲካ፣ንግድ እና ኢንቨስትመንት መስኮች ይበልጥ ለማጠናከር አሁንም በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ስቴፈን ጆቢን በበኩላቸው÷ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

አምባሳደሩ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላምን ለማጽናት እያደረጋቸው ያሉ ጥረቶች የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተግባራዊ ከማድረግ ጋር በማያያዝ አድናቆታቸውን እንደገለጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.