ወቅታዊ ቀጣናዊ ጂኦ-ፖለቲካ የደህንነት ሁኔታ ለኢትዮጵያ ደህንነት ያለው አንድምታ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወቅታዊ ቀጣናዊ ጂኦ-ፖለቲካ የደህንነት ሁኔታ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነት ያለው አንድምታ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ ላይ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዩ የፖሊሲ አማካሪ አምባሳደር ምንሊክ ዓለሙ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች፣ ምሁራንና የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በፓናሉ ላይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች እና ከመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል በተውጣጡና በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ዲፕሎማቶች፣ ምሁራንና ወታደራዊ አመራሮች የተዘጋጁ ጥናታዊ ፅሁፎች ለውይይት እንደሚቀርቡ የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል።