አየር መንገዱ 6 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው በጀት ዓመት 6 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ÷ በተያዘው በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 13 ነጥብ 7 ሚሊየን መንገደኞች ማጓጓዙን ተናግረዋል፡፡
በኮቪድ-19 ወቅት ተቋርጠው የነበሩ በረራዎችን ከመመለስ በተጨማሪ ወደ ሰባት አዳዲስ መዳረሻዎች በረራ መጀመሩንም አንስተዋል፡፡
የአውሮፕላን ቁጥርን ለማሳደግ በተሰራው ስራም 12 አዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ነው የገለጹት፡፡
በአየር መንገዱ የጥገና እና ምህንድስና ማዕከል ከመንገደኛ ወደ ጭነት አገልግሎት ሰጪነት የተቀየሩ ሁለት አውሮፕላኖች የካርጎ ስራ መጀመራቸውንም ጠቁመዋል፡፡
በበርናባስ ተስፋዬ