Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ወደ ምስራቅ ባሕር የባለስቲክ ሚሳኤልማስወንጨፏ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል፡፡

በሰሜን ኮሪያ ተተኩሷል የተባለው ሚሳኤል ወደ ምስራቅ ባህር መወንጨፉን ነው የደቡብ ኮሪያ ጦር ሹማምንቶች የገለጹት፡፡

ሀገሪቱ ሁለት የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን በተናጠል አስወነጭፋለችም ነው የተባለው፡፡

ሚሳዔሎቹ የተወነጨፉት ፒዮንግያንግ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከሚገኝበት ሱናን አካባቢ ወደ ምስራቅ ባህር (የጃፓን ባህር) አቅጣጫ እንደሆነም ተነግሯል።

የጃፓን መከላከያ ሚኒስቴር ፥ ሚሳኤሎቹ ከ528 እስከ 560 ማይል (850-900 ኪሎ ሜትር) መምዘጋቸውን እንደሚገምት ገልጿል።

ሁለቱ ሚሳኤሎች ወደ 485 ማይል አካባቢ ርቀት እንደተወነጨፉም ነው የተሰማው፡፡

አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ጥምር የባሕር ኃይል ወታደራዊ ልምምድ ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን ፥በኒውክሌር የሚንቀሳቀሰው የአሜሪካው አውሮፕላን ተሸካሚ ግዙፍ መርከብ ተሳታፊ እንደነበር ተነግሯል፡፡

ልምምዱ ለሁለት ቀናት ጀጁ በተሰኘችው የሴኡል ደቡባዊ ደሴት መካሄዱን የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

ይህን ተከትሎም ከሰሜን ኮሪያ የሚቃጣ ማንኛውንም ጥቃት በብቃት መመከት እንችላለን ሲሉ በልምምዱ ላይ ሲካፈሉ የነበሩት የደቡብ ኮሪያ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ኪም ኢን-ሆ መናጋራቸው ይታወሳል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ጊዜዎች የተለያዩ ባለስቲክ ሚሳዔሎችን በማስወንጨፍ ክንድ ሲለካኩ ቆይተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.