Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ የሚስተዋሉ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል ስምምነት ላይ ተደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ የሚስተዋሉ ሽብርተኝትን፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የአደገኛ ዕፅ እና ህገ-ወጥ የቀንድ እንስሳት ዝውውሮችን በጋራ ለመከላከል ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር እና የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ሕብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራ ልዑክ በኬንያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡

ልዑኩ በቆይታው ከኬንያው ብሄራዊ ፖሊስ አገልግሎት ኢንስፔክተር ጀነራል እና የአፍሪፖል (AFRIPOL) ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ጀነራል ጃፌት ኩሜ ጋር መወያየቱን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይቸውም÷ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች በተለይም በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ የሚስተዋሉ ሽብርተኝትን፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የአደገኛ ዕፅ እና ህገ-ወጥ የቀንድ እንስሳት ዝውውሮችን በጋራ ለመከላከል ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

በተጨማሪም ልዑኩ የኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ አገልግሎት ምክትል ኢንስፔክተር ጀነራል እና የወንጀል ምርመራ ኃላፊ መሀመድ አል አሚን ጋር ተወያይቷል፡፡

በዚህም በቢሮው ሥር የሚገኙትን የኢንቲግሬትድ ኮማንድ ሴንተር እና የፎረንሲክ ምርመራ ቢሮን የጎበኙት የልዑካን ቡድኑ አባላት÷ በቴክኖሎጂዎቹ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መስማማታቸው ተመላክቷል።

በናይሮቢ የሚገኘውን የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፅህፈት ቤት እና የፀረ ሽብር ልህቀት ማዕከልን ልዑኩ መጎብኘቱም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.