Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ዞን ከፍተኛ አመራሮች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ እና የፌዴራል ዞን ከፍተኛ አመራሮች በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል።

በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በአካዳሚው ውስጥ ‘‘ሩት ትሬነር ትሬ’’ በሚባል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የፈሉ ችግኞች መተከላቸው ተጠቁሟል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በአረንጓዴ አሻራ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብረሃም በላይ (ዶ/ር)፣ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ፈቃዱ ተሰማን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል አመራሮች በተገኙበት የችግኝ ተከላ ተከናውኗል፡፡

በተመሳሳይ በሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የተመሩ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በጋምቤላ ከተማ የችግኝ ተከላና የአቅመ ደካማ ቤት የማደስ መርሐ ግብር አከናውነዋል።

አቶ ኦርዲን በድሪ በመርሐ ግብሩ ወቅት እንዳሉት÷ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች በብዛት እና በጥራት መትከል እና መንከባከብ ከሁሉም የሚጠበቅ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.