Fana: At a Speed of Life!

ሰባት የአፍሪካ መሪዎች ለሰላም ተልዕኮ ወደ ዩክሬን አቀኑ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰባት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ለሰላም ተልዕኮ ወደ ዩክሬን ማቅናታቸው ተገልጿል፡፡

መሪዎቹ ለሰላም ተልዕኮ ነገ ወደ ሩሲያ ከማቅናታቸው በፊት በኪየቭ ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የደቡብ አፍሪካ እና የግብፅ መሪዎችን ያካተተው ቡድኑ÷ ከፕሬዚዳንት ዜለንስኪ እና ፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር የተኩስ አቁም እና ዘላቂ ሰላም መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር መስማማቱ ተመላክቷል።

የሰላም ተልዕኮው ኪየቭ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ በጀመረችበት እና ውጊያው እየጠነከረ በመጣበት ወቅት የተወጠነ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የሰላም ተልዕኮው ግጭቱን ለመፍታት ውይይት ከመጀመር እና ከዚያም ከፍ በማድረግ ሩሲያ እና ዩክሬን የጦር እስረኞችን እስከ መለዋወጥ እንዲደርሱ ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም አፍሪካን በሚመለከት እንደ እህል እና የአፈር ማዳበሪያ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ለማድረግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ጦርነቱ ከዩክሬን ወደ ውጭ የሚላከውን እህል እና ከሩሲያ የሚላከውን ማዳበሪያ በከፍተኛ ሁኔታ በመገደብ የዓለም የምግብ ዋስትና እጦትን ማባባሱ ተጠቁሟል።

ከሁለቱም ሀገራት በሚገቡ ምርቶች ላይ የተመሰረተችው አፍሪካ ደግሞ ከሁሉም ይበልጥ ጉዳት እዳስተናገደች መገለጹንም ቢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.