Fana: At a Speed of Life!

ጃፓን በጦርነቱ ለተጎዱ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ የሚውል 8 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ለትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታና የንጽህና አጠባበቅ ፕሮግራም የሚውል 8 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አደረገች።

የድጋፍ ስምምነቱን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ እና የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ አቡበከር ካምፖ(ዶ/ር) ጋር ተፈራርመዋል።

ድጋፉ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ ግጭት የወደሙ የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ያለመ እንደሆነም ነው የተጠቆመው፡፡

መሰረታዊ የሆኑ ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ትምህርት ቤቶች ያሉ ልማቶችን እና የንጽህና አጠባበቅ እና የበሽታ መከላከል ፕሮግራምን ለመደገፍ ያግዛል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

በዚህም 12 ሺህ ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ፥ የንጽህና አጠባበቅ እና በሽታ መከላከል ፕሮግራም ደግሞ 47 ሺህ የሚሆኑ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ነው የተገለጸው፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት እንደሚረዳም ተጠቁሟል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.